am_dan_text_ulb/09/24.txt

1 line
784 B
Plaintext

\v 24 ዐመፃን ለማስቆም፣ ኃጢአትን ለማስወገድ፣ በደልን ለማስተሰረይ፣ ዘላለማዊ ጽድቅን ለማምጣት፣ ራእይንና ትንቢትን ለማተምና እጅግ ቅዱስ የሆነውን ለመቀባት ስለ ሕዝብህና ስለ ተቀደሰችው ከተማህ ሰባ ሱባዔ ታውጇል። \v 25 ይህንን ዕወቅ አስተውለውም፤ ኢየሩሳሌምን ለማደስና ለመጠገን ዐዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ገዢው መሲሕ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስልሳ ሁለት ሱባዔ ይህናል። ኢየሩሳሌም ከጎዳናዎቿና ከቅጥሮቿ ጋር ትታደሳለች፤ ይህ የሚሆነው ግን በመከራ ጊዜ ነው።