am_dan_text_ulb/09/12.txt

1 line
729 B
Plaintext

\v 12 ታላቅ ጥፋት በእኛ ላይ በማምጣት፣ የተነገረውን ቃል ፈጸምህብን፤ በኢየሩሳሌም ላይ የተደረገውን የሚያህል ከሰማይ በታች ከቶ የለም። \v 13 በሙሴም ሕግ እንደ ተጻፈው፤ ይህ ሁሉ ጥፋት በእኛ ላይ ደረሰ፤ ሆኖም ከኃጢአታችን በመመለስና እውነትህን በመከተል ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ምሕረትን አልፈለግንም። \v 14 አምላካችን እግዚአብሔር በሚያደርገው ሁሉ ጻድቅ ነውና፣ በእኛ ላይ እግዚአብሔር ጥፋት ከማምጣት አልተመለሰም፣ እኛም አልታዘዝነውም።