\v 21 እየተመለክትኩም ሳለሁ ይህ ቀንድ በቅዱሳን ላይ ጦርነት ዐውጆ አሸነፋቸው። \v 22 ይህም የሆነው ጥንታዌ ጥንቱ እስኪመጣና ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪፈርድላቸው ድረስ ነበር፤ ኪዝያም የልዑሉ ቅዱሳን መንግሥቱን የሚወርሱበት ዘመን መጣ።