am_dan_text_ulb/07/19.txt

1 line
776 B
Plaintext

\v 19 ከዚያም የሚያደቅቀውንና የሚበላውን የቀረውንም ሁሉ በእግሮቹ የሚረጋግጠውን የብረት ጥርሶችና የናስ ጥፍሮች የነበሩትን ከሌሎች የተለየና እጅግ አስፈሪ የሆነውን የአራተኛውን አውሬ ምንነት የበለጠ ማወቅ ፈለግሁ። \v 20 ደግሞም በራሱ ላይ ስላሉት አሥር ቀንዶች፣ ከመካከላቸው ብቅ ስላለው ቀንድና ከዚሁ ቀንድ ፊት ስለተነቃቀሉት ሦስት ቀንዶች፣ እንደዚሁም ከሌሎች ስለበለጠው የሰው ዓይኖች የሚመስሉ ዓይኖች በትዕቢትም የሚናገር አፍ ስለነበሩት ስለዚሁ ቀንድ ማወቅ ፈለግሁ።