\v 21 ዳንኤልም እንዲህ ብሎ መለሰ፤ “ንጉሥ ሆይ፤ ለዘላለም ንገሥ፤ \v 22 ንጉሥ ሆይ፤ በፊቱ ቅን ሆኜ ስለተገኘሁ፣ በአንተም ፊት በደል ስላልተገኘብኝ አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶቹን አፍ ዘጋ፤ እነርሱም አልጎዱኝም።”