am_dan_text_ulb/06/06.txt

1 line
769 B
Plaintext

\v 6 ከዚያም የበላይ አስተዳዳሪዎቹና አሳፍንቱ ዕቅድ ካወጡ በኋላ በአንድነት ወደ ንጉሡ ሄደው እንዲህ አሉ፤ “ንጉሥ ዳርዮስ ሆይ፤ ለዘላለም ንገሥ! \v 7 ንጉሥ ሆይ፤ እስከ ሠላሳ ቀን ድረስ ወደ አንተ ካልሆነ በቀር ማንም ሰው ወደ ሌላ አምላክ መጸለይ እንደሌለበት ንጉሡ ዐዋጅ እንዲያወጣ ትእዛዙም እንዲፈጸም፤ ይህንም የተላለፈ ወደ አንበሶች ጉድጓድ እንዲጣል፣ የመንግሥት የበላይ አስተዳዳሪዎች፣ መኳንንት፣ መሳፍንት፣ አማካሪዎችና አገረ-ገዦች ሁሉ በአንድነት ተስማምተዋል፤