am_dan_text_ulb/05/05.txt

1 line
417 B
Plaintext

\v 5 በዚያን ቅጽበት የሰው እጅ ጣቶች ታዩ፤ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ በመቅረዙ ትይዩ ባለው በግድግዳው ልስን ላይ ጻፉ፤ ንጉሡም ይጽፍ የነበረውን እጅ አየ፤ \v 6 በዚያን ጊዜ የንጉሡ ፊት ተለዋወጠ በድንጋጤም ተሞላ፤ እጆቹና እግሮቹ ከዱት፤ ጉልበቶቹም ተብረከረኩ።