am_dan_text_ulb/05/01.txt

1 line
505 B
Plaintext

\c 5 \v 1 ንጉሥ ቤልሻዛር በሺህ ለሚቆጠሩ መኳንንቱ ታላቅ ግብዣ አደረገ፣ በሺሁም ፊት የወይን ጠጅ ይጠጣ ነበር። \v 2 ቤልሻዘር የወይን ጠጅ እየጠጣ ሳለ፣ አባቱ ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ ያመጣቸውን የወርቅና የብር መጠጫዎችን እርሱና መኳንንቱ፣ ሚስቶቹና ቁባቶቹ ይጠጡባቸው ዘንድ እንዲያመጡለት አዘዘ።