am_dan_text_ulb/04/31.txt

1 line
546 B
Plaintext

\v 31 ንጉሡ ይህን ገና ተናግሮ ሳይጨርስ እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ መጣ፣ “መንግሥትህ ከአንተ እንደ ተወሰደ ተነግሮአል፤ \v 32 ከሰዎች ትገለላለህ፤ መኖሪያህ ዱር ውስጥ ከአራዊት ጋር ይሆናል። እንደ በሬ ሣር ትበላለህ። ልዑል በሰዎች መንግሥት ላይ እንደሚገዛና እርሱ ለፈለገው እንደሚሰጥ እስክትገነዘብ ድረስ ሰባት ዓመታት ያልፉብሃል።”