am_dan_text_ulb/04/24.txt

1 line
653 B
Plaintext

\v 24 ንጉሥ ሆይ ትርጉሙ ይህ ነው። ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ይህ በአንተ ላይ የወጣ የልዑሉ አዋጅ ነው። \v 25 ከሰዎች መካከል ተለይተህ ትባረራለህ፥ በሜዳም ከአራዊት ጋር ትኖራለህ። እንደ በሬ ሣር እንድትበላ ትደረጋለህ፥ በሰማያትም ጠል ትረሰርሳለህ፥ ልዑሉ በአሕዛብ መንግሥታት ላይ እንደሚገዛና እንዚህንም መንግሥታት እርሱ ለወደደው ለማንም ሊሰጣቸው እንደሚችል እስክታውቅ ድረስ ሰባት ዓመታት ያልፉብሃል።