am_dan_text_ulb/04/20.txt

1 line
678 B
Plaintext

\v 20 ያየኽው ዛፍ፥ ያድግ የነበረውና የበረታው፥ ጫፉም ወደ ሰማያት የደረሰው፥ እስከ መላው ዓለም ዳርቻ ድረስ የታየው፥ \v 21 ቅጠሎቹያምሩ የነበሩት፥ ፍሬዎቹም የተትረፈረፉት፥ ስለዚህም ለሁሉ የሚሆን መብል የነበረበት፥ ከበታቹም የምድር አራዊት ጥላ ያገኙበት፥ የሰማያት አእዋፍም ይኖሩበት የነበረ፥ \v 22 ያ ዛፍ፥ እጅግ ኃያል የሆንከው ንጉሥ አንተ ነህ። ታላቅነትህ እስከ ሰማያት፥ ሥልጣንህም እስከ ምድር ዳርቻ ደረሰ።