am_dan_text_ulb/04/17.txt

1 line
818 B
Plaintext

\v 17 በመልእክተኛው በተነገረው አዋጅ ይህ ውሳኔ ሆነ። ልዑሉ በሰዎች መንግሥታት ላይ እንደሚገዛና እነዚህንም መንግሥታት ለተናቁ እጅግ ትሑታን ለሆኑ ሰዎች እንኳን ሳይቀር፥ ሊያነግሠው ለወደደው ለማንም እንደሚስጥ ሕያዋን ሁሉ ያውቁ ዘንድ ይህ የቅዱሱ ውሳኔ ነው። \v 18 እኔ ንጉሡ ናቡከደነፆር ይህን ሕልም አልሜአለሁ። አሁንም አንተ ብልጣሶር፥ በመንግሥቴ ካሉ ጠቢባን ሰዎች አንዳቸውም ሊተረጉሙልኝ አልቻሉምና ትርጉሙን ንገረኝ። አንተ የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በውስጥህ ስላለ ልትተረጉም ትችላለህ።»