\v 13 በአልጋዬ ላይ ተኝቼ ሳለሁ በአእምሮዬ አየሁ፥ አንድ ቅዱስ መልእክተኛም ከሰማያት ወረደ። \v 14 እርሱም ጮኽ፥ እንዲህም አለ፦ ዛፉንና ቅርንጫፎቹን ቁረጡ፥ ቅጠሎቹን አራግፉ፥ ፍሬውንም በትኑ። አራዊቱ ከሥሩ፥ አእዋፍም ከቅርንጫፎቹ ይሽሹ።