am_dan_text_ulb/04/10.txt

1 line
758 B
Plaintext

\v 10 በአልጋዬ ላይ ትኝቼ ሳልሁ በአእምሮዬ ያየኋቸው ራዕዮች እነዚህ ነበሩ፦ ተመለከትኩ፥ በምድርም መካከል ዛፍ ነበረ፥ቁመቱም እጅግ ታላቅ ነበረ። \v 11 ዛፉ አደገ፥በረታም። ጫፉ ሰማይ ደረሰ፥ እስከ መላው ዓለም ዳርቻ ድርስም ይታይ ነበረ። \v 12 ቅጠሎቹ ያማሩ፥ ፍሬዎቹም የተት ረፈረፉ ነበሩ፤ ለሁሉ የሚሆን ምግብም በላዩ ነበረበት። የዱር አራዊት ከበታቹ ጥላ አግኝተው ነበር፥ የሰማያት አእዋፍም በቅርንጫፎቹ ይኖሩ ነበር። ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ከእርሱ ይመገቡ ነበር።