am_dan_text_ulb/04/07.txt

1 line
747 B
Plaintext

\v 7 በዚያን ጊዜ አስማተኞች፥ሙታን ሳቢዎች፥ጠቢባንና ኮከብ ቆጣሪዎች መጡ፤ ሕልሙንም ነገርኳችው፥ ነገር ግን ሊተረጉሙልኝ አልቻሉም። \v 8 በመጨረሻም፥ እንደ አምላኬ ስም ብልጣሶር ተብሎ የተጠራውና የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያለበት ዳንኤል ገባ። ሕልሙን ነገርኩት። \v 9 «የአስማተኞች አለቃ ብልጣሶር ሆይ፦የቅዱሳን አማልክት መንፈስ እንዳለብህና የሚያስችግርህ ምሥጢር እንደሌለ አውቄአልሁና፤ በሕልሜ ምን እንዳየሁና ትርጉሙ ምን እንደሆነ ንገረኝ አልኩት።