am_dan_text_ulb/04/01.txt

1 line
582 B
Plaintext

\c 4 \v 1 ከንጉሥ ናቡከደነፆር፥በምድር ሁሉ ለሚኖሩ አሕዛብ፥ መንግሥታትና ልዩ ልዩ ቋንቋ ለሚናገሩ ሁሉ፦ «ሰላማችሁ ይብዛ። \v 2 ልዑል አምላክ ስላደረገልኝ ምልክቶችና ድንቆች እነግራችሁ ዘንድ መልካም ሆኖ ታየኝ። \v 3 ምልክቶቹ እንዴት ታላላቅ ናቸው! ድንቆቹም እንዴት ብርቱዎች ናቸው! መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፥ ግዛቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።