am_dan_text_ulb/03/26.txt

1 line
799 B
Plaintext

\v 26 ከዚያም ናቡከደነፆር ወደ እሳቱ እቶን በር ቀረቦ፦ «የልዑል አምላክ ባሪያዎች ሲድራቅ፥ ሚሳቅና አብድናጎ ኑ ውጡ! ወደዚህ ኑ!» ብሎ ተጣራ። በዚያን ጊዜም ሲድራቅ፥ ሚሳቅና አብድናጎ ከእሳቱ ውስጥ ወጡ። \v 27 በአንድነት የተሰበሰቡት የክፍላተ አገር አስተዳዳሪዎች፥ የክልል አስተዳዳሪዎች፥ ሌሎች አስተዳዳሪዎችና የንጉሡ አማካሪዎች እነዚህን ሰዎች ተመለከቱ። እሳቱ ሰውነታቸውን አልጎዳውም፥ የራሳችው ጸጉር አልተቃጠለም፥ መጎናጸፊያቸው አልተጎዳም፥ የእሳቱም ሽታ በላያቸው አልነበረም።