am_dan_text_ulb/03/21.txt

1 line
603 B
Plaintext

\v 21 እነርሱም መጎናጸፊያቸውን፥ ቀሚሳቸውን፥ ጥምጥማቸውንና ሌሎች ልብሶቻቸውን እንደ ለበሱ ታስረው ወደ ሚንቦገቦገው የእቶን እሳት ተጣሉ። \v 22 የንጉሡ ትእዛዝ ጥብቅ ስለነበረና የእቶኑ እሳት እጅግ ነዶ ስለነበረ፥ ሲድራቅን፥ ሚሳቅንና አብድናጎን የወሰዱአቸውን ሰዎች ነበልባሉ ገደላቸው። \v 23 እነዚህ ሦሥት ሰዎች እንደ ታሰሩ በሚንቦገቦገው የእቶን እሳት ውስጥ ወደቁ።