am_dan_text_ulb/03/16.txt

1 line
677 B
Plaintext

\v 16 ሲድራቅ፥ሚሳቅና አብድናጎም ለንጉሡ እንዲህ ሲሉ መለሱ፦« ናቡከደነፆር ሆይ በዚህ ጉዳይ መልስ ልንሰጥህ አያስፈልገንም። \v 17 መልስ መስጠት የሚገባን ከሆነ፥ የምናገለግለው አምላካችን ከሚንቦገቦገው የእሳት እቶን ሊያድነን ይችላል፥ ንጉሥ ሆይ፥ ከእጅህም ያድነናል። \v 18 ነገር ግን ንጉሥ ሆይ ባያድነን እንኳን፥አማልክትህን እንደማናመልክና ላቆምከውም የወርቅ ምስል እንደማንሰግድ በአንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን።