am_dan_text_ulb/03/03.txt

1 line
938 B
Plaintext

\v 3 በዚያን ጊዜም አማካሪዎችን፥ የግምጃ ቤት ኋላፊዎችን፥ ዳኞችን፥ የአጥቢያ ፈራጆችንና የክፍላተ አገር ከፍተኛ ባለ ሥልጣናትን ጨምሮ የክፍለ አገር አስተዳዳሪዎች፥ የክልል አስተዳዳሪዎችና የአካባቢ አስተዳዳሪዎች ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ በአንድነት ተሰበሰቡ። በፊቱም ቆሙ። \v 4 ከዚያም አዋጅ ነጋሪ እየጮኽ እንዲህ አለ፡- «አሕዛብ፥ መንግሥታትና ልዩ ልዩ ቋንቋ የምትናገሩ ሁሉ፥ \v 5 የመለከትና የእንቢልታ፥ የመስንቆና የክራር፥ የበገናና የዋሽንት፥ የዘፈንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ንጉሥ ናቡከደነፆር ላቆመው የወርቅ ምስል ወድቃችሁ እንድትሰግዱ ታዝዛችኋል።