am_dan_text_ulb/03/01.txt

1 line
721 B
Plaintext

\c 3 \v 1 ንጉሡ ናቡከደነፆር ርዝመቱ ስድሳ ክንድ ስፋቱ ስድስት ክንድ የሆነ የወርቅ ምስል አሠራ። በባቢሎንም ክፍለ አገር በዱራ ሜዳ አቆመው። \v 2 ከዚያም ናቡከደነፆር አማካሪዎችን፥ የግምጃ ቤት ኃላፊዎችን፥ ዳኞችን፥ የአጥቢያ ፈራጆችንና የክፍላተ አገር ከፍተኛ ባለ ሥልጣናትን ሁሉ ጨምሮ የክፍለ አገር አስተዳዳሪዎች፥ የክልል አስተዳዳሪዎችና የአካባቢ አስተዳዳሪዎች ላቆመው ምስል ምረቃ እንዲመጡ፥ በአንድ ላይ እንዲሰበሰቡ መልእክት ላከ።