am_dan_text_ulb/02/44.txt

1 line
721 B
Plaintext

\v 44 በእነዚያ ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ፈጽሞ የማይጠፋና በሌላ ሕዝብ የማይሸንፍ መንግሥት ያቆማል። ሌሎቹን መንግሥታት ይፈጫቸዋል ፈጽሞም ያጠፋቸዋል፤ እርሱ ግን ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል። \v 45 የሰው እጆች ሳይነኩት ድንጋይ ከተራራ ሲፈነቀል እንዳየህ እንዲሁ ነው። እርሱም ብረቱን፥ ናሱን፥ ሸክላውን፥ ብሩንና ወርቁን አደቀቃቸው። ንጉሥ ሆይ! ከዚህ በኋላ ሊሆን ያለውን ታላቁ አምላክ አስታውቆሃል። ሕልሙ እውነተኛ ፍቺውም የታመነ ነው።