am_dan_text_ulb/02/41.txt

1 line
753 B
Plaintext

\v 41 እግሮቹና ጣቶቹ በከፊል ከሸክላ በከፊል ከብረት ተሠርተው እንዳየህ እንዲሁ የተከፋፈለ መንግሥት ይሆናል፤ ለስላሳ ሸክላ ከብረት ጋር ተደባልቆ እንዳየህ እንዲሁ የተወሰነ የብረት ብርታት ይኖረዋል። \v 42 የእግሮቹ ጣቶች በከፊል ከብረት በከፊል ከሸክላ ተሠርተው እንዳየህ መንግሥቱ በከፊል ብርቱ በከፊል ደካማ ይሆናል። \v 43 ብረትና ለስላሳ ሸክላ ተደባልቀው እንዳየህ እንዲሁ ሕዝቡም ድብልቅ ይሆናል፤ብረትና ሸክላ እ ንደማይዋሓድ እነርሱም አብረው አይዘልቁም።