\v 25 ከዚያም አርዮክ በፍጥነት ዳንኤልን ወደ ንጉሡ አስገባና አለ፦«የንጉሡን ሕልም ትርጉም የሚገልጥ ሰው ከይሁዳ ምርኮኞች መካከል አግኝቼአለሁ። \v 26 ንጉሡም (ብልጣሶር ተብሎ የሚጠራውን) ዳንኤልን አለው፦«ያየሁትን ሕልምና ትርጉሙን ልትነግረኝ ትችላለህን?»