\v 24 ከዚህም በኋላ ዳንኤል የባቢሎንን ጠቢባን ሁሉ እንዲገድል ንጉሡ ኃላፊነት ወደ ሰጠው ወደ አርዮክ ሄደ። ሄዶም አለው፦« በባቢሎን የሚገኙትን ጠቢባን አትግድል። ወደ ንጉሡ ይዘኽኝ ግባ እኔም የሕልሙን ትርጉም ለንጉሥ እናገራለሁ።»