am_dan_text_ulb/02/14.txt

1 line
599 B
Plaintext

\v 14 በዚያን ጊዜ ዳንኤል በባቢሎን በጥበባቸው የሚታወቁትን ሁሉ ሊገድል ለመጣው ለንጉሡ የዘበኞች አዛዥ ለአርዮክ በጥንቃቄና በማስተዋል መለሰለት። \v 15 ዳንኤልም « የንጉሡ አዋጅ ለምን አስቸኳይ ሆነ?» ሲል የንጉሡን አዛዥ ጠየቀው፤ አርዮክም የሆነውን ለዳንኤል ነገረው። \v 16 በዚያን ጊዜ ዳንኤል ገባና ትርጉሙን ለንጉሡ የሚያስታውቅበት ቀጠሮ ከንጉሥ እንዲሰጠው ጠየቀ።