am_dan_text_ulb/02/10.txt

1 line
554 B
Plaintext

\v 10 ጠቢባኑም ለንጉሡ እንዲህ ሲሉ መለሱ፥«የንጉሡን ጥያቄ ሊመልስ የሚችል ሰው በምድር አይገኝም። አስማተኞችን፥ ሙታን ሳቢዎችን ወይም ጠቢባንን እንዲህ ዓይነት ጥያቄ የጠየቀ ታላቅና ኃያል ንጉሥ የለም። \v 11 ንጉሡ የሚጠይቀው ነገር አስቸጋሪ ነው፥ በሰዎች መካከል ከማይኖሩት አማልክት በስተቀር ይህንን ለንጉሡ መንገር የሚችል ማንም የለም።