am_dan_text_ulb/02/07.txt

1 line
877 B
Plaintext

\v 7 እነርሱም እንደገና እንዲህ ሲሉ መለሱ፥ «ንጉሡ ሕልሙን ለአገልጋዮቹ ይንገር፥ እኛም ትርጉሙን እንነግርሃለን።» \v 8 ንጉሡም መለሰላቸው፥ «ይህን ጉዳይ በተመለከተ ውሳኔዬ ምን ያህል ጽኑ እንደሆነ ስላወቃችሁ ተጨማሪ ጊዜ ማግኘት እንደምትፈልጉ በእርግጥ አውቃለሁ። \v 9 ነገር ግን ሕልሙን ባትነግሩኝ፥ ሁላችሁን አንድ ቅጣት ይጠብቃችኋል። ሐሰት የሆኑ አሳች አሳቦችን ለማዘጋጅት ወስናችኋል፥ አሳቤንም እስክለውጥ ድረስ ልትነግሩኝ በአንድነት ተስማምታችኋል። ስለዚህ ሕልሙን ንገሩኝ፥ ያን ጊዜም ልትተረጉሙልኝ እንደምትችሉ አውቃለሁ።»