am_dan_text_ulb/01/19.txt

1 line
652 B
Plaintext

\v 19 ንጉሡም ከእነርሱ ጋር ተነጋገረ፥አብረዋቸው ከነበሩት ሁሉ መካከል ከዳንኤል፥ሐናንያ፥ ሚሳኤልና አዛርያ ጋር የሚወዳድር ማንም አልነበረም። በንጉሡ ፊት ቆሙ፥ ሊያገለግሉት ዝግጁዎች ነበሩ። \v 20 ንጉሡ በጠየቃቸው የጥበብና የማስተዋል ጥያቄዎች ሁሉ፥በግዛቱ ሁሉ ከሚገኙ አስማተኞችና ሙታን ሳቢዎች አሥር እጥፍ በልጠው ተገኙ። \v 21 ዳንኤልም እስከ ንጉሥ ቂሮስ የመጀመሪያ ዓመት ድረስ እዚያው ነበረ።