am_dan_text_ulb/01/08.txt

2 lines
780 B
Plaintext

\v 8 ነገር ግን ዳንኤል በንጉሡ ምግብና በሚጠጣውም ወይን ራሱን እንዳያረክስ በውስጡ አሰበ። ራሱን እንዳያረክስ ከዋናው አለቃ ፈቃድ ጠየቀ። \v 9 ዋና አለቃው ለእርሱ ባለው አክብሮት አማካይነት እግዚአብሔር ለዳንኤል ሞገስንና ጸጋን ሰጠው። \v 10 ዋና አለቃውም ዳንኤልን አለው፥
« እኔ ጌታዬን ንጉሥን እፈራለሁ። ምን ዓይነት ምግብና መጥጥ ማግኘት እንዳለባችሁ አዞኛል። በእናንተ እድሜ ካሉ ወጣቶች ይልቅ ከስታችሁ ስለ ምን ይመለከታል? ንጉሡ ከእናንተ የተነሳ በሞት ይቀጣኝ ይሆናል።»