\v 6 ከእነዚህም መካከል አንዳንድ የይሁዳ ሰዎች፥ ዳንኤል፥ አናንያ፥ ሚሳኤልና አዛሪያ ነበሩ። \v 7 ዋና አለቃውም ስም አወጣላቸው፦ ዳንኤልን ብልጣሶር፥ አናንያን ሲድራቅ፥ ሚሳኤልን ሚሳቅ፥ አዛሪያንም አብድናጎ ብሎ ጠራቸው።