am_dan_text_ulb/01/01.txt

1 line
655 B
Plaintext

\c 1 \v 1 በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት በሦሥተኛው ዓመት፥አቅርቦቶቿን ሁሉ ለማስቆም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፥ ከበባትም። \v 2 ጌታም ለናቡከደነፆር በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአቄም ላይ ድል ሰጠው፥እርሱም ከእግዚአብሔር ቤት የተቀድሱ ዕቃዎች ጥቂቱን ሰጠው። እርሱም ወደ ባቢሎን ምድር፥ ወደ አምላኩ ቤት አመጣቸው፥የተቀደሱትንም ዕቃዎች በአምላኩ ግምጃ ቤት ውስጥ አኖራቸው።