am_col_text_ulb/03/01.txt

1 line
609 B
Plaintext

\c 3 \v 1 እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ከሞት ካስነሣችሁ፤ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያሉትን ነገሮች እሹ። \v 2 በላይ ስላሉት ነገሮች እንጂ በምድር ስላሉት ነገሮች አታስቡ። \v 3 ምክንያቱም ሞታችኋል፤ ሕይወታችሁንም እግዚአብሔር በክርስቶስ ውስጥ ሰውሮታልና። \v 4 ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እናንተም ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ።