|
\c 2 \v 1 ስለ እናንተና በሎዶቅያ ስላሉት ሰዎች እንዲሁም ፊቴን በሥጋ አይተውት ስለማያውቁ ስለ ብዙዎች ምን ያህል ብርቱ ትግል እንዳደረግሁ እንድታውቁ እወዳለሁ። \v 2 ልባቸው ተጽናንቶና በፍቅር ተሳሰረው ፍጹም የሆነ የመረዳት ብልጽግና እንዲኖራቸውና የእግዚአብሔርን ምስጢር የሆነውን እውነት ክርስቶስን እንዲያውቁ እታገላለሁ። \v 3 የጥበብና የዕውቀት ሀብት ሁሉ የተሰወረው በእርሱ ነው። |