|
\c 7 \v 1 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ። እነሆ፥የጸደይ አዝመራ መብቀል በሚጀምርበት ጊዜ የአንበጣን መንጋ ፈጠረ፥ ተመለከትሁም፥ ከንጉሥ አጨዳ በኋላ ዘግይቶ የበቀለ አዝመራ ነበር። \v 2 የምድሪቱን ሣር በልተው ከጨረሱ በኋላ፤ «ጌታ እግዚአብሔር ሆይ እባክህ ይቅር በል፥ ያዕቆብ በዚህ ውስጥ እንዴት ይቆማል? እርሱ ታናሽ ነውና» አልሁ። \v 3 እግዚአብሔርም ስለዚህ ነገር ተጸጸተ፤ «ይህ አይሆንም» አለ። |