am_amo_text_ulb/07/04.txt

2 lines
615 B
Plaintext

\v 4 \v 5 \v 6 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ፦እነሆ፥ጌታ እግዚአብሔር በእሳት ለመፍረድ ጠራ። እርሱም በምድር ውስጥ የሚገኘው ን ሰፊና ጥልቅ ውኃ አደረቀ፥ምድሪቱንም ደግሞ በላ። እኔ ግን፦«ጌታ እግዚአብሔር ሆይ እባክህ ተው፥ያዕቆብ በዚህ ውስጥ እንዴት ይቆማል? እርሱ ታናሽ
ነውና» አልሁ። እግዚአብሔርም ስለዚህ ነገር ተጸጸተ፤«ይህም ደግሞ አይሆንም» ይላል ጌታ እግዚአብሔር።