\v 3 የጥፋትን ቀን ለምታርቁ፥የግፍንም መንበር ለምታቀርቡ ወዮላችሁ! \v 4 ከዝሆን ጥርስ በተሠሩ አልጋዎች ላይ ይተኛሉ፥በመከዳዎቻቸውም ላይ ይዝናናሉ። ከበጎች መንጋ ጠቦትን፥ከበረትም ጥጃን ይበላሉ።