\c 4 \v 1 እናንተ የባሳን ላሞች፥በሰማሪያ ተራራ የምትኖሩ፥ድኾችን የምትጨቁኑ፥ችግረኞችን የምታደቅቁ፥ባሎቻችሁንም «መጠጥ አምጡልን» የምትሉ ይህን ቃል ስሙ። \v 2 ጌታ እግዚአብሔር በቅድስናው እንዲህ ብሎ ምሎአል፦«ተመልከቱ፥እናንተን በመንጠቆ፥የቀሩትንም በዓሳ መንጠቆ የ ሚወስዱበት ቀናት ይመጣል።