\v 4 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ «የእግዚአብሔርን ሕግ ጥለዋልና፥ ትእዛዙንም አለጠበቁምና ስለ ሦሥት የይሁዳ ኃጢአቶች፥ይልቁንም ስል አራቱ፥ ቅጣቴን አልመልስም። ሐሰታቸው አስቷቸዋልና፥በዚሁ መንገድ አባቶቻቸውም ሄዱ። \v 5 እሳት በይሁዳ ላይ እልካለሁ፥ የኢየሩሳሌምንም ምሽጎች ይበላል።