\v 14 በረባት ቅጥሮች ላይ እሳት አነድዳለሁ፥ በጦርነት ቀን ከጩኽት ጋር፥ በአውሎ ነፋስም ቀን ከማዕበል ጋር፤ አብያተ መንግሥትን ይበላል። \v 15 ንጉሣቸው ከአለቆቻቸው ጋር ወደ ምርኮ ይሄዳል» ይላል እግዚአብሔር።