am_amo_text_ulb/08/01.txt

1 line
681 B
Plaintext

\c 8 \v 1 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ፤ የበጋ ፍሬ ቅርጫት ተመለከትሁ! \v 2 እርሱም፥ «አሞጽ፥ ምን ታያለህ?» አለኝ። እኔም፥ «የበጋ ፍሬ ቅርጫት» አልሁት። ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ «በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ፍጻሜ መጥቶአል፤ ከእንግዲህ ወዲያ አልምራቸውም። \v 3 የቤተ መቅደሱ ዝማሬ ዋይታ ይሆናል። የጌታ እግዚአብሔር አዋጅ ይህ ነው፥ በዚያን ቀን፥ «አስከሬኑ ብዙ ይሆናል፤ በሁሉ ሥፍራ በዝምታ ይጥሏቸዋል።»