am_amo_text_ulb/05/18.txt

1 line
561 B
Plaintext

\v 18 የእግዚአብሔርን ቀን ለምትፈልጉ ወዮላችሁ! የእግዚአብሔርን ቀን ለምን ትፈልጋላችሁ? ጨለማ ነው እንጂ ብርሃን አይደለም። \v 19 አንድ ሰው ከአንበሳ ሲሸሽ ድብ እንደሚያጋጥመው፥ ወደ ቤት ገብቶ እጁን ግድግዳ ላይ ሲያስደግፍ እባብ እንደሚነድፈው ነው። \v 20 የእግዚአብሔር ቀን ብርሃን ሳይሆን ጨለማ አይደለምን? ብሩህ ሳይሆን ደብዛዛ አይደለምን?