am_amo_text_ulb/04/06.txt

1 line
606 B
Plaintext

\v 6 የጥርስ ንፃትን በከተማዎቻችሁ ሁሉ፥ እንጀራንም ማጣትን በስፍራዎቻችሁ ሁሉ እሰጣችኋለሁ። እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም ---- ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።» \v 7 ለመከር ሦሥት ወር ሲቀረው ዝናብ ከለከልኋችሁ። በአንዱ ከተማ ላይ እንዲዘንብ፥ በሌላውም ከተማ ላይ እንዳይዘንብ አደረግሁ። በአንዱ ቁራጭ መሬት ላይ ዘነበበት፥ ያልዘነበበት ቁራጭ መሬት ግን ደረቀ።