am_amo_text_udb/02/07.txt

2 lines
993 B
Plaintext

\v 7 ድኾችን በጭቃ ውስጥ ረገጧቸው፤ ለረዳት አልባዎችም ፍትሐዊ አያያዝ አላደረጉላቸውም፡፡ ወንዶች ልጆችና አባቶቻቸው ከተሸጠች አንዲት ባሪያ ሴት ጋር በመተኛት እኔን አዋርዶውኛል፡፡
\v 8 8. ድኾች ሰዎች ገንዘብ በሚበደሩበት ጊዜ አበዳሪዎቹ እነዚያን ሰዎች ገንዘቡን መመለስ እስከሚችሉ መያዣ የሚሆን ልብስ እንዲሰጧቸው ያስገድዷቸዋል፡፡ ነገር ግን በእያንዳንዱ ቀን መጨረሻ እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው ያንን ልብስ በመመለስ ፋንታ አማልክታቸውን በሚያመልኩባቸው ስፍራዎች በዚያ ልብስ ላይ ይተኙበታል! በተለያዩ ምክንያቶች ሰዎች ገንዘብ እንዲከፍሏቸው ያደርጋሉ፤ ከዚያ በኃላ በአማልክታቸው መቅደስ ይጠጣሉ፡፡