am_amo_text_udb/04/04.txt

1 line
1.0 KiB
Plaintext

\v 4 እኔን የሚያመልኩ ብዙ ሰዎች ወዳሉባቸው በቤቴልና በጌልጌላ ወዳሉ የኮረብታ ጫፍ የጣዖታት ማምለኪያ ስፍራዎች ተነሥታችሁ ሂዱ፤ በእኔ ላይም የምታደርጉትን ዓመፅ አብልጣችሁ ፈጽሙ እዚያም በደረሳችሁ በማግሥቱ መሥዋዕቶቻችሁን አቅርቡ፣ በማግሥቱም የእህላችሁን ዐሥራት አምጡልኝ፡፡ \v 5 ለእኔ ምስጋና ለማቅረብ የኅብስት መባዎችን እንደዚሁም ማቅረብ የሌለባችሁን ሌሎች መባዎችን አቅርቡ፤ ከዚያም ስላቀረባችኋቸው ስለ እነዚህ መባዎች በትምክህት ተናገሩ፤ ምክንያቱም ማድረግ የምትወዱት ይህንን ነውና፤ ይህንን የምታደርጉት ሌሎችን ለማስደነቅ ነው እንጂ እኔን ደስ ለማሰኘት አይደለም፤ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬዋለሁና ይህ በእርግጥ እውነት ነው፡፡