1 line
823 B
Plaintext
1 line
823 B
Plaintext
\c 4 \v 1 በባሳን አውራጃ እንዳሉ የሰቡ ላሞች እየወፈራችሁ ያላችሁ እናንተ ባለጠጋ የሰማርያ ሴቶች፣ ድኾችን ትጨቊናላችሁ፤ የተቸገሩ ሰዎችንም ታሠቃያላችሁ ለባሎቻችሁም፡- ‹‹የምንጠጣውን ብዙ ወይን ጠጅ አምጡልን!›› ትሏቸዋላችሁ፡፡ \v 2 ነገር ግን እግዚአብሔር አምላካችን እንደዚህ ብሏል፡- ‹‹እኔ ቅዱስ ነኝና ይህንን ተስፋ አስረግጬ እናገራለሁ፡- እናንተ ሁላችሁም ወደ ሌላ አገር የምትወሰዱበት ጊዜ ፈጥኖ ይደርሳል፣ ጠላቶቻችሁ እናንተን የሚይዙባቸው የተሳሉ መንጠቆዎችን እየተጠቀሙ፣ ይወስዷችኋል፡፡ |