\v 3 ያመልጡ ዘንድ ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ጫፍ ቢወጡም ፈልጌ እይዛቸዋለሁ፤ ወደ ባሕሩ ጥልቅ በመውረድ ከእኔ ለመደበቅ ቢሞክሩም ትልቅ የባሕር አውሬ እንዲነክሳቸው አዛለሁ፡፡
\v 4 ጠላቶቻቸው ቢይዟቸውና ወደ ሌሎች አገሮች እንዲሄዱ ቢያስገድዷቸው በዚያ በሰይፍ እንዲገደሉ አዛለሁ፤ ልረዳቸው ሳይሆን ላስወግዳቸው ቈርጫለሁ፡፡››