am_amo_text_udb/04/10.txt

2 lines
1.0 KiB
Plaintext

\v 10 በግብፅ ሕዝብ ላይ እንደላክኋቸው ያሉ መቅሠፍቶች እንዲደርሱባችሁ አደረግሁ፤ ብዙ ወጣቶቻችሁ በጦርነት እንዲሞቱ አደረግሁ፤ ፈረሶቻችሁንም ጠላቶቻችሁ እንዲማርኳቸው ፈቀድሁ፤ ከወታደሮቻችሁ ብዙዎቹ ተገደሉ፤ ሰፈራችሁም በእነርሱ አስክሬን ጠረን ተሞላ፤ እንደዚህ ባደርግባችሁም እናንተ ግን እኔን ተዋችሁኝ፤ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬዋለሁና ይህ በእርግጥ ይፈጸማል!
\v 11 እንደ ሰዶም እንደ ገሞራ ሕዝብ ብዙዎቻችሁን አስወገድኋችሁ፤ ያልሞታችሁት እናንተ ጨርሶ እንዳይነድ ከእሳት ውስጥ እንደተነጠቀ ትንታግ ነበራችሁ፤ ይህንን ባደርግባችሁም እናንተ ግን ተዋችሁኝ፡፡ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬዋለሁና ይህ በእርግጥ ይፈጸማል!