am_amo_text_udb/08/09.txt

2 lines
726 B
Plaintext

\v 9 ሕዝቤን በምቀጣበት በዚያን ጊዜ ፀሐይ በቀትር እንድትጠልቅ አደርጋለሁ፣ ምድርም በመላ በቀን ይጨልማል፡፡
\v 10 መንፈሳዊ በዓሎቻችሁንም የምታለቅሱባቸው ቀናት አደርጋቸዋለሁ፣ ከመዘመር ይልቅ ሁሉም ሰው ያለቅሳል፤ ከማደርገው ነገር የተነሣ ሐዘናችሁን ለመግለጽ ሁላችሁም ማቅ ትለብሳላች፣ ራሳችሁንም ትላጫላችሁ፤ ያንን ቀን ሰዎች አንድያ ልጅ ሲሞትባቸው እንደሚያለቅሱበት ጊዜ አደርገዋለሁ፡፡ በዚያን ጊዜ ሁሉ ሁላችሁም በጣም ታዝናላችሁ፡፡