am_amo_text_udb/07/04.txt

3 lines
862 B
Plaintext

\v 4 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር በሌላ ራዕይ ያሳየኝ ይህንን ነበር እርሱ እሳት እንዲመጣና ሕዝን እንዲቀጣ ይጠራል፡፡ በራዕዩ እሳቱ በምድሪቱ በሞላ የነበረውን ውሃ ሲያደርቅ በምድሪቱም ላይ የነበረውን ማንኛውንም ነገር ሲያቃጥል አየሁ፡፡
\v 5 ከዚያ በኋላም እንደገና እንዲህ ብዬ አለቀስሁ፡- ‹‹እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ እባክህ ይህን እንድታስቆመው እማፀናለሁ! እኛ የእስራኤል ሕዝቦች እጅግ ምስኪኖች ነን፣ እንዴት ልንቋቋመው እንችላለን?
\v 6 ስለዚህ እግዚአብሔር እንደገና ሃሳቡን በመለውጥ ‹‹ይህም ደግሞ አይሆንም›› አለ፡፡